ወደ ዜና ይመለሱ

ሰበር ዜና ፦ ታሪካዊው የአርጤምስ 2 ተልዕኮ በስኬት ተጠናቀቀ፡ ጠፈርተኞቹ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ በሰላም አረፉ

ሰበር ዜና ፦ ታሪካዊው የአርጤምስ 2 ተልዕኮ በስኬት ተጠናቀቀ፡ ጠፈርተኞቹ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ በሰላም አረፉ

የናሳ እና የካናዳ ስፔስ ኤጀንሲ ጠፈርተኞች ከ10 ቀናት ታሪካዊ የሕዋ ላይ ቆይታ በኋላ፣ በሀገራችን ሰዓት አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት ላይ በፓስፊክ ውቅያኖስ ውስጥ በሰላም አርፈዋል። "ኦሪዮን" የተሰኘውን መንኮራኩር የተጠቀመው ይህ የአርጤምስ 2 ተልዕኮ፣ ከ1972ቱ የአፖሎ 17 (Apollo 17) ተልዕኮ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጨረቃ የተመለሱ ጠፈርተኞች ያረፉበት ሲሆን፤ የሰው ልጅ ዳግም ወደ ጨረቃ እና ማርስ ለሚያደርገው ቀጣይ ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ከፋች ሆኗል።

የናሳ እና የካናዳ ስፔስ ኤጀንሲ ጠፈርተኞች ከ10 ቀናት ታሪካዊ የሕዋ ላይ ቆይታ በኋላ፣ በሀገራችን ሰዓት አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት ላይ በፓስፊክ ውቅያኖስ ውስጥ በሰላም አርፈዋል። "ኦሪዮን" የተሰኘውን መንኮራኩር የተጠቀመው ይህ የአርጤምስ 2 ተልዕኮ፣ ከ1972ቱ የአፖሎ 17 (Apollo 17) ተልዕኮ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጨረቃ የተመለሱ ጠፈርተኞች ያረፉበት ሲሆን፤ የሰው ልጅ ዳግም ወደ ጨረቃ እና ማርስ ለሚያደርገው ቀጣይ ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ከፋች ሆኗል።

የተልዕኮው ዋና ዋና ክንውኖች፣ አዲስ ሪከርድ እና ታሪካዊ ስብጥር

አራት ጠፈርተኞችን የያዘው ይህ ተልዕኮ ወደ ጨረቃ በመጓዝ እና በዙሪያዋ በማንዣበብ ስኬታማ ሙከራዎችን አድርጓል። ይህ ቡድን በታሪክ ልዩ የሚያደርገው ስብጥሩ ነው፤ በጉዞው ላይ ወደ ጨረቃ በመጓዝ ታሪክ የሰሩት የመጀመሪያዋ ሴት ጠፈርተኛ ክሪስቲና ኮክ፣ የመጀመሪያው ጥቁር ጠፈርተኛ ቪክቶር ግሎቨር፣ እና የመጀመሪያው ካናዳዊ ጠፈርተኛ ጀረሚ ሀንሰን እንዲሁም የተልዕኮው አዛዥ ሪድ ዋይስማን ተሳትፈዋል።

ከዚህም ባሻገር ተልዕኮው አዲስ ታሪክ ጽፏል። ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት እ.ኤ.አ በ1970 በአፖሎ 13 ተይዞ የነበረውን የ400,171 ኪ.ሜ ሪከርድ በመስበር፣ ከምድር ከ422,000 ኪሎሜትሮች በላይ በመራቅ የሰው ልጅ ወደ ጠፈር ጠልቆ የገባበትን አዲስ የርቀት መጠን አስመዝግቧል።

ጠፈርተኞቹ ከዚህ ታሪካዊ ጉዞ ለሳይንስ የሚጠቅሙ በርካታ መረጃዎችን፣ ምስሎችን እና ጠቃሚ ጥናቶችን ይዘው በሰላም ተመልሰዋል።

የአርጤምስ 2 ዋና አላማ እና ስለ አርጤምስ 3 እቅድ

ይህ የ10 ቀናት ተልዕኮ ዋነኛ አላማ የኦሪዮን መንኮራኩርን የህይወት ድጋፍ ስርዓቶች በተግባር መፈተሽ ነበር። ብዙዎች እንደሚያስቡት ቀጣዩ "አርጤምስ 3" ተልዕኮ ጠፈርተኞችን በቀጥታ ጨረቃ ላይ አያሳርፍም። ይልቁንም እ.ኤ.አ በ2027 እንዲካሄድ የታቀደው አርጤምስ 3፣ በዝቅተኛ የምድር ምህዋር ላይ በመሆን በኦሪዮን እና እንደ ስፔስ ኤክስ እና ብሉ ኦሪጅን ባሉ የግል ኩባንያዎች የጠፈር መንኮራኩሮች መካከል የመገጣጠም እና ሌሎች የዝግጅት ስራዎችን ለመሞከር የተነደፈ ነው።

ከማረፍ በፊት የነበረው ዝግጅት እና ጥብቅ የአየር ሁኔታ

ይህ ማረፍ (Splashdown) የተሳካ እንዲሆን ጥብቅ የአየር ንብረት ሁኔታዎች መሟላት ነበረባቸው፤ ከእነዚህም ውስጥ የውቅያኖሱ ማዕበል ቁመት ከ1.8 ሜትር በታች መሆን፣ የነፋስ ፍጥነት ከ46 ኪ.ሜ/ሰአት አለመብለጥ እና በማረፊያው 30 ኖቲካል ማይል ዙሪያ ዝናብም ሆነ መብረቅ አለመኖሩ ይገኙበታል።

ኢንተግሪቲ ወደ ከባቢ አየር ስትገባ የሚያሳይ ምስል ከመንኮራኩሩ ላይ የተነሳ

መንኮራኩሯ ወደ ምድር ከባቢ አየር ከመግባቷ 42 ደቂቃዎች በፊት፣ አላስፈላጊው የአገልግሎት ክፍል (Service module) ተገንጥሎ በከባቢ አየር ውስጥ እንዲቃጠል የተደረገ ሲሆን፤ የጠፈርተኞቹ ክፍል (Crew module) ብቻ የሙቀት መከላከያውን ወደ ፊት በማድረግ ቀሪውን ጉዞ አጠናቋል።

እጅግ አደገኛው ወደ ከባቢ አየር የመግባት ሂደት እና የሙቀት መከላከያው

መንኮራኩሯ ወደ ምድር ስትመለስ በ00:07 GMT ላይ በሳን ዲዬጎ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ በስኬት አርፋለች። ነገር ግን ይህ ሂደት እጅግ አደገኛ ነበር። ኦሪዮን ወደ ምድር ከባቢ አየር ስትገባ በሰዓት 38,300 ኪ.ሜ (ከድምጽ ፍጥነት 32 እጥፍ) በሚደርስ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ትጓዝ ነበር።

ኢንተግሪቲ የድምጽን 33 ዕጥፍ ፈጥና ስትጓዝ የሚፈጠረው ፕላዝማ የሙቀት መከላከያዋን ሲያቃጥለው የሚያሳይ ምናባዊ ሲሙሌሽን

በዚህ ፍጥነት አየሩን ሰንጥቃ ስትገባ በሚፈጠረው ግጭት ምክንያት እስከ 2,700 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚደርስ፣ ከእሳተ ገሞራ የሚበልጥ ከፍተኛ ሙቀት ተፈጥሮ ነበር። ይህን የተቋቋመው "አቭኮት" (Avcoat) ከተባለ ልዩ ማቴሪያል የተሰራው የሙቀት መከላከያ (Heat shield) ነው። ይህ መከላከያ ሙቀቱን በመምጠጥ ቀስ በቀስ እየተቃጠለ እና እየረገፈ (ablative) ጠፈርተኞቹን ይታደጋቸዋል። በእዚህ የመግባት ሂደት ውስጥ ጠፈርተኞቹ በመደበኛው የመሬት ስበት ላይ (Gravity) እስከ 7 እጥፍ የሚደርስ ከባድ ጫና (G-force) አሳልፈዋል፤ ይህም ማለት 100 ኪሎግራም የሚመዝን ሰው 700 ኪሎግራም ያህል ክብደት እንዲሰማው ያደርጋል ማለት ነው።

የግንኙነት መቋረጥ እና የስኬት ማረፊያ

መንኮራኩሯ ከባቢ አየር ውስጥ ስትገባ በዙሪያዋ በተፈጠረው ከፍተኛ የፕላዝማ (plasma) ንብርብር ምክንያት፣ ከገቡ 24 ሰከንዶች በኋላ (ልክ በ 23:53:24 GMT ላይ) ከመቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር የነበረው የሬዲዮ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ነበር። ይህ የግንኙነት መቋረጥ (Blackout period) ለ6 ደቂቃዎች ያህል የቆየ ሲሆን፣ ወቅት እጅግ አስጨናቂው የተልዕኮው ክፍል ነበር።

ኢንተግሪቲ ወደ ከባቢ አየር ስትገባ የታየን የመጨረሻው ምስል ፤ ግንኙነት የተቋረጠው በከባቢ አየር እና በመንኮራሩር ካፕሱሉ መሃል በተፈጠረው እፍጋት ምክኒያት ባለው ፕላዝማ ነው

ከዚያም 11 ያህል ተከታታይ ፓራሹቶች በተያዘላቸው ሰዓት በመከፈት ፍጥነቱን ከከፍተኛ ደረጃ ወደ 32 ኪ.ሜ በሰዓት በማውረድ በሰላም ውሃው ላይ አሳርፈዋታል። ማረፊያዋ ላይ ሲደርሱም ዩ.ኤስ.ኤስ ጆን ፒ መርታ (USS John P Murtha) የተባለችው የባህር ኃይል መርከብ እና ሄሊኮፕተሮች ጠፈርተኞቹን በፍጥነት ከውቅያኖሱ አውጥተዋቸዋል።

ኢንተግሪቲ ፍጥነቋን እንትቀንስ ያገዙዋት ፓራሹቶች

ጠፈርተኞቹ በመርከቧ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ፣ በሂውስተን ወደሚገኘው የናሳ ጆንሰን ስፔስ ማዕከል (Johnson Space Center) በሰላም ተመልሰዋል።


ሰዎች እነዚህንም ወደዋል