ናሳ በይፋ 'ሄሎ፣ ዓለም" ብሎ የሰየመው አስደናቂ ፎቶግራፍ እ.ኤ.አ ከ1972 የአፖሎ 17 ቡድን በኋላ በሰው ልጅ የተነሳው የምድራችን የመጀመሪያ ፎቶግራፍ ሆነ።
ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ ዓይኖች ከጥልቅ ጠፈር ወደ ምድር እየተመለከቱ ነው። እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 1፣ 2026 ከኬኔዲ የጠፈር ማዕከል የተነሳው የናሳ አርቴሚስ 2 ተልዕኮው የሰው ልጅን ወሰን ከመግፋት ባለፈ በህዋ ውስጥ ያለንን ቦታ የሚያሳይ አስደናቂ አዲስ የፎቶ አልበም ለሰው ልጅ አበርክቷል።

Hello, World. NASA
"ሄሎ፣ ዓለም"
የአርቴሚስ 2 ተልዕኮ አዛዥ ሬድ ዊዝማን የኒኮን D5 ካሜራ ሌንሱን በኦሪዮን ካፕሱል መስኮት በኩል ወደ ምድር አመለከተ። ናሳ በይፋ "ሄሎ፣ ዓለም" ብሎ የሰየመውን አስደናቂ ፎቶግራፍም አነሳ። ይህ ፎቶግራፍ የአፖሎ 17 ቡድን እ.ኤ.አ በ1972 "ሰማያዊ እብነ በረድ" ተብሎ ስያሜ ከተሰጠው ምስል በኋላ ከዝቅተኛ የምድር ምህዋር ባሻገር በሰው ልጅ የተነሳው የምድራችን የመጀመሪያ ፎቶግራፍ ሆነ።
ፎቶውን ከኢንፎግራፊክ ጎን ለጎን በመተንተን፣ ምስሉ ላይ ያሉትን ቦታዎች እና ልዩ ባህሪያትን መለየት እነችላለን፡-
ቬኑስ፡- ከምድር በላይኛው ግራ ጠርዝ ባሻገር ባለው ሰፊ የጠፈር ጨለማ ውስጥ የሚያበራ ትንሽ፣ ደማቅ ነጥብ።
የዞዲያክ ብርሃን፡- ወደ ጠፈር የሚዘረጋ ደካማ፣ ጭጋጋማ ብርሃን፣ በፕላኔቶች መካከል ካለው አቧራ የሚያንፀባርቅ የፀሐይ ብርሃን።
የምድር ከባቢ አየር፡- ምድር ፀሐይን ስትሸፍን በጫፉ ላይ በሚያምር ሁኔታ የሚያብረቀርቅ ቀጭን ግርዶሽ ብርሀን።
የአውሮራ ብርሃን፡- በምድር የላይኛው ቀኝ እና የታችኛው ግራ ጠርዝ ላይ በግልጽ የሚያበሩ።
የሌሊት ከተማ መብራቶች፡- የአፍሪካን አህጉር እና የላይቤሪያን ባሕረ ገብ መሬት ከታች በግራ በኩል በግልጽ ተለይተው የሚታዩ ናቸው።

"Hello, World" Image info-graphics of what we see on the image (NASA/Reid Wiseman)
ግልፅ ለማረግ ያህል ከላይ የተብራራው የአርቴሚስ 2 "ሄሎ፣ ዓለም" ምስል ሰሜን ወደ ላይ እንዲያመለክት ለመትንተን ሲባል ተገልብጧል::
የ'ሄሎ፣ ዓለም' ምስል ሜታዳታ ከ51200 ISO በላይ ሲያሳይ ምንም እንኳን ምድር ፀሀይን ብትሸፍንም በጨረቃ ብርሃን እና በISOው ምስሉ በርሀንን ትላብሷል።
በዲጂታል ፎቶግራፍ ISO ጨለም ላሉ ቦታዎች ይበልጥ ብርሃን እንዲኖረው ያረጋል:: ሆኖም፣ የአውሮራዎችን እና የከተማ ፍርግርግ ደካማ ብርሃንን ቢያጎላም፣ "ዲጂታል ጫጫታ" በመባል የሚታወቀውን የኤሌክትሮኒክ ጣልቃ ገብነትንም ጨምሮ ያጎላል። ይህ በአርቴሚስ 2 ምስል ላይ እንደሚታየው የተበታተኑ፣ ትናንሽ የሆኑ ፒክስሎች ናቸው። ምስሉ ላይ የሚታዩት ደቃቅ ነጠብጣቦች አብረቅራቂውን ከባቢ አየር እና ከመቶ ሺ ኪ.ሜ በላይ ርቀት ላይ ያሉ የከተማ መብራቶችን ፤ አስደናቂ ታይቶ የማይታወቅ እይታን ለማንሳት የተከፈለ አነስተኛ ዋጋ ነው።

Illuminated in Orion NASA
ከጠፈር ጨለማ ምድርን መምረጥ:
በጠፈር መንኮራኩሩ መስኮቶች ላይ ብርሃን እንዳያንፀባርቅ እና ጥራቱን የጠበቀ ፎቶግራፎችን ለመቅረጽ፣ ናሳ ሳይንትስቶቹን የካፕሱሉን መብራቶች እንዲያጠፉ ምክር ሰጥቷቸዋል።
ናሳ በዚህ ጉዞ ላይ እየለቀቃቸው ካሉ ፎቶዎች መካከል የተልዕኮ ባለሙያ የሆነችው ክርስቲና ኮች በተንቀሳቃሽ ግላዊ ኮምፒውተሯ (PCD) ላይ ስትሰራ፣ ከጎኗ ደግሞ የካናዳ የጠፈር ማእከል የተልዕኮ ባለሙያ ጄርሚ ሃንሰን በኦሪዮን የጠፈር መንኮራኩር (ቅጽል ስሙ ኢንቴግሪቲ) መስኮት በኩል ወደ ውጭ ሲመለከት ያለበት ይገኛል።
የዚህ ተልዕኮ እና ጉዞ ስሜታዊ ክብደት በክሪስትና ኮች በትክክል ተግልጿል። ለጨረቃ ጉዞ የተሳካ የሞተር (TLI) የቲ ኤል አይ ቃጠሎን ተከትሎ፣ ለተልእኮ ቁጥጥር በሬዲዮ መልዕክት አስተላልፋለች፡-
“ይህ የሞተር ቃጠሎ ሲቃጠል፣ ምድርን ትተን አንሄድም ። ምድርን እንመርጣታለን እንጂ"

Hello, Moon NASA
የአርቴሚስ 2 ቡድን ወደ ጨረቃ ጉዞው ላይ ለአምስተኛው ቀን በረራ ሲጀምር፣ በኦሪዮን ሶላር ፓናል ጫፍ ላይ የተገጠሙ ውጫዊ ካሜራዎች ጨረቃ እየቀረበች ስትሄድ ያለበት ምስል ወደ ምድር ብዙ ልኳል፡፡ ጨረቃን በሩቅኛው ክፍል በኩል ለመብረር ሲደርሱ፣ የአርቴሚስ 2 ብዱን በመፈራረቅ የመጀመሪያው የሆነውን ፎቶ አንስተዋል፡፡
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መላው የኦሪየንታሌ ተፋሰስ (orientale basin) በቀጥታ በሰው ዓይን ታይቷል። በጨረቃ የቅርብ እና ሩቅ ክፍል መካከል ባለው ድንበር ላይ የሚገኘው ይህ ግዙፍ፣ ባለብዙ ቀለበት ተፋሰስ 930 ኪ.ሜ ስፋት ያለው ሲሆን ከ3.8 ቢሊዮን ዓመታት በፊት በአስከፊ አስትሮይድ ድብደባ የተፈጠረ ነው። ከኦሪዮን የሚላከው ምስል ልዩ ከሚያረግበት ምክንያት ውስጥ አንዱ ፥ የጠፈር መንኮራኩሩ እየበረረበት ያለበት ስፍራ እና ርቀት ከማንኛውም ቀደምት የጨረቃ ተልእኮዎች ይልቅ ጨረቃን በተሻለ ሁኔታ አርቴሚስ 2 እንዲመለከት እድል ሰጥቶታል።

NASA
ናሳ ታሪክ በመሰራት ላይ ነው። ኦሪዮን ወደ ምድር ለመመለስ እንደ ወንጭፍ የጨረቃን የስበት ኃይል በመጠቀም የበረራ መንገዱን በተሳካ ሁኔታ አስተካክሎ እየተመለሰ ይገኛል።
በሚቀጥሉት ቀናት፣ እነዚህ አራት የጠፈር ተመራማሪዎች ስለ አጽናፈ ዓለም ያላቸውን ታሪካዊ አመለካከት ማጋራታቸውን ሲቀጥሉ፣ ዓለም ደሞ እንሱ በሰላም እንዲመለሱ ጓግቶ ይጠብቃል፡፡